በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን::
አባታችን ጻድቁ አቡነ ስነ ኢየሱስ የትውልድ አገራቸው ሰሜን ሸዋ ደብረ ብርሃን ልዩ ቦታው ልብሆ ከአባታቸው አብርሃም ከ እናታቸው አስካለ ማርያም ይባላሉ ጻድቁ ስነ ኢየሱስ በምናኔ ገዳመ ዋፊት ገብተው ማህበሩን ሲያገለግሉ ለብዙ ጊዜ ከቆዩ በኋላ ከ አቡነ ዮሐንስ እጅ ምንኩስናን ተቀብለዋል:: ከዚያም በቅዱስ ገብርኤል መሪነት በእግዚአብሄር ፈቃድ ወደ ሰሜን ጎንደር አርማጭሆ በመሄድ የወርቅ ለብሆ ቅዱስ ያዕቆብ ዝግሙድ የተባለው ገዳም እንደገና አቅንተው በተጋድሎ ለብዙ ጊዜ ሲጋደሉ ኖረዋል ጻድቁ ስነ ኢየሱስ በህይወታቸው ዘመን ሁሉ በትሩፋትና በተጋድሎ ሰውነታቸውን ከአጥንታቸው ጋር እስኪጣበቅ ድረስ ስጋደሉ መኖራቸው በገድላቸው ተዘግቦ ይገኛል በዚህም ክቡር ቅዱስ ዳዊት የጻድቅ ሰው ሞቱ እረፍቱ ነው እንደሚለው መስከረም አንድ ቀን መላከ ሞት ከሰማይ ወደ እሳቸው መቷል:: ጻድቁም እግዚአብሄር በሰጣቸው ፀጋ ወደ እሳቸው መምጣቱን ስለተረዱ ለምን መጣህ ብለው ሲጠይቁት ታዞ መምጣቱን ሲገልፅላቸው የወዳጄ ቅዱስ ገብርኤል የወርና የዓመት በአሉን ሳላከብር አልሄድም በማለት ገዝተው አቁመውታል:: ከቆመበት ሳይነቃነቅ ከመስከረም 1 ቀን እስከ ታህሳስ 19 ቀን እንደቆመ ሳይንቀሳቀስ ዝክራቸውን ዘክረው እንደፈጸሙ ክብር ምስጋና ይግባውና ጌታችን መድሀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ታህሳስ 19 ቀን ካዕላፍ መላዕክት ከሐዋርያት: ከጻድቃን:ከሰማእታት:ከነእንጦስ ከነመቃርስ:ከደናግል መነኮሳት እንዲሁም ከእናቱ ቅድስተ ቅዱሳን ቅድስት ድንግል ማርያም ጋር በመሆን ከቦታው በመውረድ በአለም የደከመ ሁሉ ለዘላለም ይድናል እንዳለው ወደጄ ልጄ ስነ ኢየሱስ ሆይ ስለ ስሜ መከራ ተቀብለህ እንዳስደሰትከኝ እኔም ደስ ላሰኝህ ልታዘዝህ እነሆ አለሁኝ አላቸው:: ጻድቁም በትህትና እንደ አንተ ቸርነት እንጂ እንደ እኔ ስራ አይደለም ብለው በፍርሀትና በመጨነቅ ወደ ምድር ወደቁ አምላካችንም ጻድቁን አንስቶ የከበረውን ነፍሳቸውን በተቀደሱ እጆቹ ተቀብሎ ስምህን ለጠራ ዝክርህን ለዘከረ በእረፍትህ ቀን እጣን መብራት መባ ላመጣ አንተ ከገባህበት ዘላለማዊ ቤትህ አገባቸዋለሁ:: ቦታህን ሊሳለም የመጣውን ኢየሩሳሌም እንደሄደ እቆጥርለታለሁ:: ሐጢያቱን ለካህን ለመናገር አሳፍሮት የበዛ ሐጢያቱን አባታችን አቡነ ስነ ኢየሱስ 3 ጊዜ ይቅር በለኝ ቢል ሐጢያቱን እደመስስለታለሁ:: ለክብርህ ቀን እንጨት የለቀመውን ውሃ የቀዳውን ከንጹሃን አርድህቶችህ እደምራቸዋለሁ:: በቦታህ ከወደቀው ፍርፋሪ እንኳን በስምህ የወደቀውን ምግብ ቢመገብ ስጋ ወደሙ እንደተቀበለ አደርግለታለሁ:: የእጀ ሰብ ስራይ ተደርጎበት የመቃብርህን አፈር አዋህዶ ቢረጨው ስራዩን እፈታለታለሁ:: በሬም ላምም ቢሆን ቢታመምበት በስምህ ጻድቁ ስነ ኢየሱስ ብሎ ቢማጸን በደልና ሐጢያቱን እደመስስለታለሁ:: አንተን አምኖ ከቦታህ ላይ ቢቀበር ከሰሳ ወቀሳ ሳይኖርበት በክብሬና በመንግስቴ ለዘላለም ከእኔ ጋር ይኖራል:: ቦታህን እየረዳ ያረፈውን እንደ ሰማእቱ ቅዱስ ጊዮርጊስ በሰማእትነት እቆጥረዋለሁ:: ቦታህን ለአንዲት ቀንም ስያልፍም ቢሆን የረገጠ 12 ትውልዱን እምርለታለሁ::በጉልበቱ በገንዘቡ በእውቀቱ ወጥቶ ወርዶ የሚራዳውን በክብርህ ቀን የሚዘምረውን በእግሩ ደክሞ ቦታህን ረግጦ ያከበረህን ራሱ ድኖ ለወገኖቹ 60 ትውልድ ከሲኦል አወጣለታለሁ ብሎ እውነት እንጂ ሐሰት በማይታበለው ቃሉ ቃል ኪዳን ሰጥቶአቸው በምስጋና በእልልታ በክብር መንግስቱ ወደ ሰማይ አርጓል:: ቅዱሳን ልጆቻቸው በክብር ገንዘው ከቤተመቅደስ ውስጥ በሳጥን የጻድቁ አጽም ይገኛል ዛሬም ምንም በአካለ ስጋ ቢለዩም ከቦታቸው ላይ ለበቁ አባቶች በአካለ ነፍስ በመገለጽ ቦታቸውን አስከብረውት ይገኛሉ::
ጻድቁ ስነ ኢየሱስ ቀን የሰሩትን ቤተክርስቲያን ሌሊት እየመጣ ጨለማ ለብሶ ፈላሻ የተባለ ጽረ ቤተክርስቲያን እያፈራረሱባቸው ሲያዝኑና ሲተክዙ እግዚአብሄር ባወቀ በ እግዚአብሄር ፈቃድ ዋልክዳ ከሚባል ቦታ አውሬ አዳኝ ወደገዳሙ በመምጣት አጋዘኗን በጥይት መቷት ደሟን እያዘራች ጻዲቁ ቆመው ከሚጸልዩበት እግራቸው ስር ወድቃለች አዳኙም ፈለጓንና ደሟን ተከትሎ ከወደቀችበት ሲደርስ ጻዲቁ ስነ ኢየሱስ ብርሃን ተጎናጽፎ በሚያስፈራ ግርማ ሲመለከታቸው ፈጥኖ ወደ መሬት ወድቋል:: ጻዲቁም በአበው ስርአት ሰውም ሆነ አውሬ መግደል ወንጀል ሐጢያት ነው በማለት ገስጸው መክረው አስተምረው ለሁለተኛ ጊዜ እንዲህ አይነት ስራ እንዳይደግምህ ተጠንቀቅ ብለው ከአሳሰቡት በኋላ ለአሁኑ የመታሃትን አጋዘን ፈቅጄልሃለሁ ባርከህ ተጠቀምባት ስሉት አዳኙም ስጋዋን አወራርዶ እንደጨረሰ ታላቅንና ታናሹን ለጻድቁ ሊሰጣቸው ስሞክር እግዛብሄር ያዘዘኝ በአርምሞና በጸሎት እንድጋደል እንጂ ሥጋ በልቼ በመንፈስ ደካማ እንድሆን አይደለም:: አንተ ግን የአንተ ልጆች ለእኔ ልጆች ግዳይ ባደረጉ ጊዜ ታላቅና ታናሽ ለገዳሙ በመስጠት በረከት እንዲቀበሉ ስርአት ይሁንላችሁ ሲሉ ተናግረውታል:: አሁን ግን አንተን የምጠይቅህናንድ ጉዳይ አለኝ ቀን የምሰራውን ማታ የሚያፈርስብኝ ሰጣን ያደረባቸው ፈላሾችን እንድታጠፋልኝ ፈቃድህ ይሁን ሲሉ ጠይቀውታል ጻድቁ ስነ ኢየሱስም ፈጣሪዬን ስባዬ ገብቼ ከጠየኩ በኋላ እኔ ስነግርህ የምገባውን ትዕዛዝ ታደርጋለህ በዚህም መሰረት ሱባዬ ገብተው ሲጨርሱ ያንን አዳኝ ለጻዲቁ ጥቃት መወጣት የተላከ መሆኑን ስለተረዱ የ እግዚአብሄር ሃይል ታጥቀህ ድል እንደምታደርጋቸው አምላኬ ነግሮኛል አዳኙም ጻድቁ በጸሎት የሰጡትን ግዳጅ በደስታ ተቀብሎ ንቂት ከተባለው ቦታ በድንገት ደርሶዐያነቀ ድል አድርጓቸዋል:; አዳኙም ወደ ገዳሙ በማቅናት ጠላቶቹን ድል በማድረጉ እያበሰረ ከጻድቁ ፊት ደርሳል ጻድቁ ስነ ኢየሱስም እግዚአብሄር በሰጣቸው ጸጋ ድል እንዳደረጋቸው ተመልክተው መነኮሳቱን አሰልፈው በደስታና በዝማሬ ተቀብለውታል:: ጻድቁም ከዛሬ ጀምሮ ከልጆቼ መነኮሳት አንድነት ደምሬሃለሁ እንደ አንድ ሰው ምከር ብለው መካሪያን ተብላል::
የወርቅ ለብሆ ቅዱስ ያዕቆብ ዘግሙድ ገዳም አመሰራረት
በሰሜን ጎንደር ሀገረ ስብከት በታች አርማጭሆ በሣንጃ ወረዳ በደብረ ሲና ቀበሌ የሚገኝ ገዳም ሲሆን በኢትዮጵያ ከርዕሰ ገዳማት አንዱ ነው በዚህ መሠረት በዮዲት ጉዲት ዘመን ቤተክርስቲያኑ ተቃጥሏል ከዚያም ጊዜ ጀምሮ ለብዙ ዘመን ጠፍ ሆኖ ስኖር ጻድቁ ስነ ኢየሱስ ከገዳመ ዋፊት በመልአኩ ቅዱስ ገብር ኤል እየተመሩ በራዕይ አምደ ብርሃን ከሰማይ ወደ ምድር ከሚያርፉበት ቦታ ተተክሎ አይተዋል:: ተጋድሎህን እግዚአብሄር በዚህ ቦታ በስምህ ብዙ የመንፈስ ቅዱስ ልጆች የሚወለዱበት አጽምህ የምፈልስበት ቦታ መሆኑን ስለተረዱ በ 1210 ዓ/ም በአጼ ይስሐቅ ዘመነ መንግስት አባታችን ስነ ኢየሱስ ይህን ገዳም ገድመውታል:: ከተገደመጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ 797 ዓመታትን አስቆጥራል:: ጽድቁ ስነ ኢየሱስም አቦ ገዳም እየተባለ ከሚጠራው ቦታ ቆመው ሲጸልዩ ከቆሙ ሳይቀመጡ እጃቸውን ከዘረጉ ሳያጥፉ ለ 7አመት ለድህነት ምክንያት የሆነ ፀበል ፈልቆላቸው በጸበሉ አጋንንት ያደረባቸውን የተለያዩ ደዌ ያለባቸውን ሁሉ እየተፈወሱበት ይገኛል:: የፈጣሪኢያቸውን ቸርነት እያመሰገኑ ወደ ሰሃአራአ ገዳም በመሄድ ለ 3 አመት በሱባኤ እንደቆዩ ቦታው ለልጆቻቸው ጾር ላሳቀቃቸው ደዌ ለጸናባቸው ማረፊያ በህርመት ፆም ለቆዩ የሚገድፉበትን መሆኑን ተረድተው ለ3ኛ ጊዜ ገድመውታል:: በገዳሙ ውስጥ በግራኝ ጊዜ 320 መነኮሳት በአቦ ገዳም 83 መነኮሳት ሰሀራ ገዳም 96 መነኮሳት ተሰይፈው አልፈዋል:: ቦታውም የሰማእታት ቦታ እየተባለ ይጠራል ጻድቁ ስነ ኢየሱስ በገዳሙ ውስጥ ለ 300 አመት ከ አንዲት የምሶብ ቅርጽ ካላት ድንጋይ ላይ ቆመው ጸልየዋል ከቆሙበት ድንጋይ ስርም 2ኛ ጸበል ፈልቆቸው ብዙ ገቢረ ተዐምር ሲደረግበት እንደነበር በገድሉ ተመዝግቦ ይገኛል በጸበሉም በበሽታው አይነት እውራኖች ሲያይበት መስማት የተሳናቸው ሲሰሙበት መካን የነበሩ የማይወልዱ ሲወልዱበት የስካር በሽታ ሲዱንበት ለምጻሞች ሲነጹበት አንካሶች ሲረቱበት የነቀርሳ ኪንታሮት ሌሎችም መስል በሽታዎች በጻድቁ እምነትና ጸበል እንዲሁም መኮሬታ በመጠቀም እየተፈወሱ ይገኛሉ በእጀሰብ በስራይ የተያዙ እንዲሁም በዘመኑ በሽታ ኤድስና ካንሰር የተበከሉ ብዙ ወንድሞችና እህቶች ድነውበት በቦታው ምስክርነት እየሰጡ ይገኛሉ:: በገዳሙ ውስጥ በርካታ አባቶች በ እጃቸው የፈለፈሉት ብዙ ዋሻ ይገኛሉ:: ዛሬም ብዙ መነኮሳቶች ከስው ተለይተው ማህበሩ ፈቅዶላቸው በጽሞናና በአርምሞ የሚኖሩ አባቶች በገዳሙ ዘግተው ይገኛሉ:: ጻድቁ ስነ ኢየሱስ በመላእክት ከሰማይ የወረደላቸው አንድ የድንግልና አንድ የተጋድሎ አክሊል በክብር በመቅደስ ይገኛል:: የጻድቁ አጽምና በሳቸው እግር የተኩት አቡነ የማነ ክርስቶስ አጽም ብዙ ገቢረ ተአምር እያደረገ ዘወትር በጸሎት እጣን እየታጠኑ ይገኛሉ በጻድቁ ስነ ኢየሱስ እጅ የተባረከ የመልአኩ ገብርኤል ታቦትና የማህበረ በኩር ጽላት በየዓመት በአላቸው እየተቀደሰባቸው ይገኛል::
ጻድቁ ስነ ኢየሱስ ካረፉ በምትካቸው አቡነ የማነ ክርስቶስ የተባሉ ልጃቸው ተሹመዋል አቡነ የማነ ክርስቶስም የአባታቸውን ፈለግ በመከተል በመንፈስ ቅዱስ የተቃኙ በመሆናቸው በአጼ ሱስንዮስ ዘመነ መንግስት ጊዜ ንጉሱ ሃይማኖታቸውን ከኦርቶዶክስ እምነት ውጪ በመውጣታቸው አንደበታቸው ተዘግቶ አጼ ፋሲልም የአባታቸውን ችግር በጸሎት ከእግዚአብሄር ምህረት እንዲስጣቸው ሲማጸኑ መባም የሚያስፈልገውን ለገዳሙ ቃል ገብተዋል አበው መነኮሳትም ሌሊት በሰዓታት ቀን በዳዊት በመፀለይ የእግዚአብሄር ቸርነት ተገልጾላቸው ከመሰል የመንፈስ ቅዱስ ወንድሞቻቸው ጋር በመሆን ስጋ ወደሙ ቀድሰው ሲያቀብላቸው ተመዞ የነበረው ምላሳቸው ወደነበረበት ሊመለስ ችሏል:: በዚህም በመደሰት ለገዳሙ መተዳደሪያ 44 ቅፈፍ ጉልት ተቀብልው እንደነበር ገዳሙ አስራት እያስከፈለ ሣንጃ ወረዳን እራሱ እንደሚያስተዳድር ታሪካቸው ያስረዳል::
የእግዚአብሄር ክብርና ምስጋና ይሁንና የአባታችን የጻዲቁ ስነ ኢየሱስ እና የቅዱስ ያዕቆብ ዘግሙድ አንድነት ገዳም ቃል ኪዳን ከብዙው ባጭሩ ከዚህ ላይ ተፈጸመ አነሳስቶ ላስጀመረን አስጀምሮ ላስፈጸመን ለቸሩ አምላካችን መድሃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ክብርና ምስጋና ለእሱ ይሁን:: writing by deme ad