በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሀዱ አምላክ አሜን::
ወር
በገባ በ29 በቤተክርስቲያናችን ታስበው ከሚውሉት እግዚአብሔር አምላክ ቃል ኪዳን ከገባላቸውን ከሰጣቸው እናቶች
ኢትዮጵያዊቷ ሰማዕትና ጻድቅ ቅድስት ፍቅርተ ክርስቶስ /እመ እሙዝ/ ትገኛለች ታዲያ ፍቅርተ ክርስቶስ /እመ እሙዝ/
ማን ናት? ምን ቃል ኪዳን ተሰጣት? እናም ደረገችውን ተጋድሎ በጥቂቱ እንመልከት
ጻድቃን በጻድቅ ስም የሚቀበል የጻድቁን ዋጋ ይወስዳል፡፡ ማቴ. 10፡40-42
በሰሜን ወሎ ሀገረ ስብከት በመቂት ወረዳ ጥባ ማርያም ቀበሌ ውስጥ ምን ታምር በመትባል ቦታ ላይ በ16ኛው መቶ ክፍለ ዘመን በኢትዮጵያዊቷ ሰማዕትና ጻድቅ ቅድስት ፍቅርተ ክርስቶስ የተመሰረተቸው እመ ምዑዝ ኪዳነ

ምህት
ቅድስት ፍቅርተ ክርስቶስ አንድት ገዳም ትገኛለች፡፡ ይህች ገዳም ከአዲስ አበባ በደሴ ወደ ጎንደር በሚወስደው
መንገድ 665 ኪሎ ሜትር ከተጓዙ በኋላ ገራገር/ ፍላቂት/ ከምትባለው ከተማ በመውረዱ በእግር 2፡30 /ሁለት ሰዓት
ከሰላሳ ደቂቃ / እንድተጓዙ ከ370 ዓመት ባለይ ያስቆጠረቸውን እመ ምዑዝ ኪዳነምህት ቅድስት ፍቅርተ ክርስቶ
በአንድ ቀን የሠራቻትና ለጌታ በአራቱም አቅጣጫ የሰገደችውን ታላቅና ድንቅ ቤተመቅደስ ያገኛሉ ፡፡ የዚህች ታላቅ
ገዳም መሰራች ኢትዮጵያዊቷ ሰማዕትና ፃድቅ ቅድስት ፍቅርተ ክርስቶስ አንድነት ገዳም ያገኛሉ፡፡ የዚህች ታላቅ ገዳም
መስራች ኢትጵያዊት ሰማዕትና ጻድቅ ቅድስት ፍቅርተ ክርስቶስ በደቡብ ጎንደር ደራ ፎገራ አንበሳሜ ወረዳ ልዩ ስሙ
አቡነ ሐራ ገዳም አዋሳኝ ከተታ ማርያም ተብሎ በሚጠራ ቦታ በሚያዚያ 4 /አራት/ቀን ተፀንሳ ታህሳስ 29 / ሃያ
ዘጠኝ/ ቀን በጌታ ልደት ተወለደች፡፡ አባቷ ላባ እናትዋ ወንጌላዊት የተባሉ እግዚዘብሔርን የሚወዱ ትዕዛዙን
የሚከብሩ ደጋግ ሰዎች ነበሩ፡፡ መሀን ሆነው ልጅ ባመውለዳቸው እያዘኑ ተግተው ወደ እግዚአብሔር በመፀለያቸው ቅድስት
ፍቅርተ ክርስቶስን የመሰለች የልጅ እናት በፀሎተዋ ለሀገር ለወገን የምትበቃ ሰጥቷቸዋል፡፡ ከዚይም 80/ሰሚኒያ
ቀን / ሲሆናት ለልጅነት ጥምቀት ወደ ቤተ መቅደስ በወሰዷት ጊዜ ከጥምቀት በኋላ ስጋ አምላክ ስትቀበል /ስትቆርብ/
ሕይወት የሆነውን ቅዱስ ስጋህን ክቡር ደምህን የሰጠኸኝ አምላኬ ክብር ምስጋና ይግባህ ብላ አመስግናለች፡፡ ስመ
ክርስትናዋ ማርያም ፀዳለ ሲሆን የአለም ስሟ ሙዚት ነው፡፡ ፍቅርተ ክርስቶስ የምንኩስና /የቆብ/ ስሟ ነው፡፡
እናታችን ቅድስት ፍቅርተ ክርስቶስ አባ ዳንኤል ከሚባል አባት መፅሐፍን እየተማረች ካደገች በኋላ ለአቅመ ሄዋን ስትደርስ እናትና አባቷ ሊድሯት በመፈለጋቸው ዘርዓ ክርስቶስ ለሚባል ከደጋግ ሰዎች ወገን ለሆነ ሰው አጋቧት ፡፡ ማታ እንደ ሙሽሮች ደምብ ወደ ጫጉላ ቤት ሲገቡ ቅድስት ፍቅርተ ክርስቶስ ቅደሱ ዘርዓ ክርስቶን ወንድሜ ሆይ እኔ የእናት አባቴን ፍቃድ ለመፈፀም ነው እንጂ ስጋዊ ሙሽራ መሆን አልፈልግም ፡፡ ፍላጎቴ የእግአብሔት ሙሽራ መሆን ነው በማለት ብታማክረው ቅዱስ ዘርዓ ክርስቶስም ፀጋ እግዚአብሔት የበዛለት ሰው ነበርና እኔም እናት አባቴን ላክበር ፈቃዳቸውን ለመፈፀም ነው እንጂ የስጋ ፈቃድ የለኝም በማለት ከተነጋገሩ በኋላ በአንድ ቤት ውስጥ ለቤተሰቦቻቸውን ለአገሬው እንደ ባልና ሚስት ግን በንፅህና ለ40/ አርባ አመት / ሁለቱም በድንግልና ኖረዋል፡፡ ከዚያም በኋላ በእግዚአብሔር ፈቃድ ቅዱስ ሚካኤል መጥቶ ወንድ ልጅ እንደሚወልዱ ቢግራቸውም ሁለቱም ይህስ አይሆንም ብለው ለ40 /አርባ ቀን / በጾም ፀሎት በትጋት ጸልየዋል፡፡ መልአኩ ተገልጦ ይህ የእግዚአብሔ ፈቃድ ነው ሁለታችሁም ድንግልናችሁ አይፍስም ብሎ ነግሮአቸዋል፡፡ ከዚያም ወንድ ልጅ ወልደዋል ህፃኑ በተወለደ በ7/ሰባት/ ዓመቱ በቅዱስ ሚካኤል እቅፍ ገነትን ለ7 /ሰባት/ ቀናት ከጎበኛ በኋላ ወደ ምድር ሲመልሰው በእናት አባቴ አምላክ ይዤሃለሁ ወደዚች ወደ ከፋች ከረፋች ዓለም አትመልሰኝ ብሎ ቢለምነው ቅዱስ ሚካኤልም ከአምላክ ጠይቆ በብሔረ ህያዋን የህፃናት አለቃ ተብሎ እንዲቀመጥ አድርጎታ ፡፡ ስሙም ዳግማዊ ቂርቆስ ተብሏል፡፡
ቅድስት ፍቅርተ ክርስቶና ቅዱስ ዘርዓ ክርስቶስም ልጅ ከወለዱ በኋላ እንደ ቀደሞው በቅድስና በንፀህና ፀንተው ኑረዋል፡፡ በዘመናቸው በኢትዮጵያ ነግሶ የነበረው ንጉስ አፄ ሱስንዮስ ሃይማኖቱን ለውጦ ሁለት ባህርይ የሚሉ ካቶሊኮችን በመቀበሉ ክርስቲያኖችን እየገደለ ነው የሚል ወሬ ሰምተው ወደ ንጉ በመሄድ ሳይፈሩ ስለ ተዋህዶ ሃማኖታቸው በንጉ ፊት መስክረዋል፡፡ ንሱም በጣም የበዛ መከራን አድርሶባቸዋል፡፡ መከራ በበዛ ቁጥር እነርሱም እየፀኑ ተከታዮቻቸውንና የንጉሰን ሠራዎቶች ሳይቀር እያሳመኑ ቢያስቸግት በሰማዕትነት ከተቀበሉት ውስጥ የማሕበር ስለሴው ጻድቁ አምደ ስላሴ የጎረጎሪ ማርያም አባ መርአዊ የመሲ ኪዳነ ምህረቷ እመ ወተት እና ከ60 , 0000 /ስልሳ ሺህ / ባይ ክርሰቲኖች ሰማዕትነት ተቀብለዋል፡፡
ቅድስት ፍቅርተ ክርስቶስ ቅዱስ ዘርዓ ክርስቶስም ልጅ ከወለዱ በኃላ እንደ ቀድሞው በቅድስና በንጽህና ጸንተው ኑረዋል፡፡በዘመናቸው በኢትዮጵያ ነግሶ የነበረው ንጉስ አጼ ሱስንዮስ ሃይማትን ለውጡ ሁለት ባህሪይ የሚሉ ካቶሊኮችን በመቀበሉ ክርስቲያኖችን እየሀደለ ነው የሚል ወሬ ሰምተው ወደ ንጉስ በመሄድ ሳይፈሩ ስለ ተዋሕዶ ሀይማታቸው በንጉስ ፊት መስክረዋል፡፡ንጉሱም በጣም የበዛ መከራ አድርሶባቸዋል፡፡ መከራ በበዛ ቁጥር እነርሱም እየጸኑ ተከታዮቻቸውንና የንጉሱን ሰራዊቶች እያሳመኑ ቢያስቸግሩ በሰማዕትነት አንገታቸውን አስቆርቷቸዋል፡፡አንገታቸውም ሲቆረጥ ከሁለቱም ደም ውሃ ወተት ፈሷዋል፡፡በዚያን ዘመን ከእነ ቅድስት ፍቅርተ ክርስቶስ ጋር ሰማዕትነት ከተቀበሉት ውስጥ የማህበረ ስላሴው ጻድቁ አምደ ስላሴ የጎረጉር ማርያም አባ መርአዊ የመሲ ኪዳነ ምህረት እመ ወተት እና ከ60 ሺ በላይ ክርስቲያኖች ሰማዕትነት ተቀብለዋል፡፡
ቅድስት ፍቅርተ ክርስቶስ አንገቷ ከተቆረጠና ሰማእትነት ከተቀበለች በኋላ ወደ ምድር መልሶ አንገቷን ከቀሪው የሰውነተዋ ክፍል ጋር አዋህዶ ከአንቅልፍ አንደሚነቃ ሰው ቀስቅሶ አስነስቷቷል፡፡ ከዚያም አቡነማርቆስ ስርዓተ ምንኩስናን በመቀበል ዋልድባ ገዳም ለ4 /አራት/ ዓመት አገልግላለች፡፡ ከዚም ከ500 /አምስት መቶ/ የሚበልጡ ተከታዮችዋን መነኮሳትን አስከትላ በሰሜን ወሎ ቆቦ ወረዳ ወደምትገኘውና በፃድቁ በአባ ጉባ ተመስርታ ጠፍታ ወደ ነበረችው ራማ ኪደና ምህረት አንድነት ገዳም በመሄድ ገዳሟን አቅንታ የወንድ የሴት ብላ ስርዐዓት ሰርታ ገዳሟን አስተካክላ 500/አምስት መቶ የሚሆኑ አገልጋች መነኮሳትን አኑራ ወደ ኢየሩሳሌም ጉዞ ጀምራለች፡፡በመንገዷም ላይ በላኤተ-ሰብ / ሰውን የሚበሉ / ወደ ሚኖሩበት አካባቢ በመድረስ እነርሱም እርሷንና 60/ ስልሳ/ የሚሆኑ አገልጋዮችዋን በጉጠት በማውጣት አራት /4/ ወራት በጨለማ ቤት ውስጥ ዘግተውባቸዋል፡፡ ከአራት ወር በኋዋላም በዓል አድገው ለመብላት ከቤት ቢያወጧቸው መልካቸው እንደ ፀሐይ የሚያበራ ቢሀንባቸው አንቺ ሴት ምንድን ናችሁ ብለው ጠይቀዋታል፡፡ እርሷም ክርሰቲያን መሆናቸውናና እነሱ የስላሴ ሕንፃ የሆነውን የሰውን ልጅ መብላት እንዴለባቸው ብትመክቸው ምን አንብላ ብለዋታል ፡፡ እርሷም ከራማ ኪዳነ ምህረት ስትነሳ የእህል ዘርን በአገከልጋዮቿ አሲዛ ነበርና ስንዴው በአንድ ቀን ዘርታ በቅሎ ታጭዶ ደርቆ ተፈጭቶ ለምግብነት በቅቷል፡፡/ ደርሷል/ ፡፡ እርሷ ቀምሳ ብታቀምሳቸው እንደማር እንደ ወተት የሚጣፍጥ ሆኖላቸው በደስታ ተመግበውታል፡፡ ከዚያም እንደዚህ እያደረጉ እየሰሩ እንዲበሉ አስተምራ አስጠምቃ ከ6/ስድስት/ የሚበልጡ አብያተ ክርስቲያናትን አስተክላላቸዋለች ፡፡ ከዚያም የተወሰኑ አገልጋዮችን አስቀምጣላቸው ወደ ኢየሩሳሌም በመሄድ ለ7 ዓመታት በአየሩሳሌም ከኖረች በኋላ የአመቤታችን በዓል ለማክበር ወደ ግብፅ በመሄድ ላይ ሳለች በመንገድ አንድ ቤተክርስቲየን ውስጥ ገብታ ስትፀልይ እመቤታችን በስዕሏ ላይ ተገልጣ ቦታዋ በኢትዮጵያ መሆኑን ነግራ እጇን ዘርግታ ወደ ኢትዮጵያ ሂጂ ብላ ከነገረቻት በኋላ በብርሃን አምድና በቅዱስ ሚካኤል እየተመራች አሁን ወደ ምትታወቅበትና የእግዚአብሔት ድንቅ ሥራ ወደ ተገለፀበት እመ ምዑዝ ኪዳነ ምህረት ቅድስት ፍቅርተ ክርስቶስ አንድነት ገዳም ደርሳለች፡፡ በቦታው ስትደርስ የቦታው ልምላሜ የሚያስደስት ነበርና ይህች ቦታ ምንታምር ብላለች፡፡ ቦታውም እስከ አሁን ደረስ ምንታምር በመባል ይጠራል፡፡ ምንታምር ላይ ከአገልጋዮቿ ጋር በመሆን አርፋ ሳለ ከኢየሩሳሌም መርቶ ያመጣት የብርሃን አምድ በዚያ ቦታ ላይ በስፋት ረቦ / ከምድር እስከ ሰማ ተተክሎ/ ብታየው መልአኩም ቦታሽ ይሄ ነው ብሎ ቢነግራት በዚያው ተቀምጣለች፡፡ የቦታው ባለአባት ይህን ቦታ ልቀቂ ቢሎ ቢጠይቃት እግዚአብሔር የሰጠኝ ቦታዬ ነው ብላዋለች፡፡ እርሱም ለክስ ወደ ጎንደር በመሄድ ንጉስ አፄ ሱስንዮስ አርፈው አፄ ፋሲል ነግሰው ነበርና እሳቸውን ፍርድ ቢጠይቃቸው በዝና ያውቋት ነበርና ቤተክርሰቲያን ካልተሰራ ትልቀቅልህ ከተሠራ ግን ሌላ ቦታ ይሰጥሃል የሚል ፍርድ አስፈርዶ ሲመልስ ቅዱስ ሚካኤል ቀድሞ ቶሎ ቤተክርሲቲያን ስሪ እንዲህ የሚል ፍርድ ተፈርዷል ብሎ ነግሯት ‹‹ ታህሳስ 14 ቀን ከነግህ ፀሎት በኋላ በሰንሰልና በስሚዛ ግድግዳዋን በአይጥ ሀረግ ማገር አድርጋ የግድግዳ ቤተ መቅደስ በዕለተ አርብ በአንድ ቀን ሰርታ ታህሳስ 16 ቀን እሁድ ታቦተ ኪዳነ ምህረትን አስገብታ ቅዳሴ አስቀድሳለች ›› ቅዳሴውም ከተፈፀመ በኋላ ጌታቸውን ከቅዱስ መንበሩ ላይ እንዳለ ሆኖ ከእናቱ ከእመቤታችን ጋራ ታያቸው፡፡ ከመንበሩ ወርዶም ይህን ቦታ በባረከው ጊዜ የስሚዛው ቤተመቅደስ በአራቱም አቅጣጫ ለፈጣሪው ሰገደ፡፡ የመሬት መናወጥም ሆነ ቅድስት ፍቅርተ ክርስቶስም ልታጠፋን መጣህን ቤተክርሰቲያኔንስ ልታፈርሳት ነው ; ብላ ብትጠይቀው ይህ የሰንሰል ቤተመቅደስሽ ዳግም እስከምመጣ ድረስ ሳፈርስ ሳይታደስ ፀንቶ ይኖራል፣ በውስጡም እስከ ዓለም ፍፃሜ ድረስ የክሀድያንና ፣ መናፍቃን እግር አይገባበትም፣ በውስጧ ቁርባንን የተቀበሉ ሁለ ኃጢያታቸው ይሰረይላቸዋል፣ ዘወትር ምህረቴ በረከቴ ከእነርሱ ጋር ይኖራል በማለት ተናግሮ ተሰወራቸው፡፡
ከዚያም በኋላ መነኮሳትና መነኮሳይያት ቅድስት ፍቅርተ ክርስቶስን የትሩፋት ዜናዋን ሰምተው ከየአቅጣጫው ተሰበሰቡ፡፡ ቅድስት ፍቅርተ ክርስቶስም በአምላክ ሀይል ተጋድሎአቸውን ይፈፅሙ ዘንድ ታስተምራቸው ፣ ትመክራቸው፣ በተግባርም እያሳየቻቸው ለብዙ ዘመናት ከኖሩ በኋላ በገዳሙ ላይ የአጋንንት ፆር እንዳይነሳ ወንዶቹን ለብቻ ሴቶቹን ለብቻ አደረገች፡፡ ዘወትርም እንዳይተያዩ የእግዚአብሔት መልዐክ በቅድስተ ፍቅርተ ክርሰቶስ ፀሎት ይጠብቃቸው ነበር፡፡
ከዚህ በኋላ እናታችን ቅድስት ፍቅርተ ክርስቶስ ከዚህ ኃላፊ ዓለም መለየቷ በቀረበ ጊዜ ሁለት መላዕክት ወደ እርሷ መጥተው በብርሃን ሰረገላ ጭነው ወደ ደብረ ነባት ይኸውም ወደ ብሔረ- ህያዋ ወስደው በዚያ ቅዱስ ቁርባንን አቀብለው ወደ ቦታዎ መለሷት፡፡ መልዐኩም ከጻማ ከድካም ከመታረዝ ከረሐብ ከጥም ከመትጋት ከእንባ በሌሊትና በቀን ከመጮህ ከዚህ ዓለም የምትለይበት ጊዜ እነሆ ደረሰ አላት፡፡
የካቲት 27 ቀንም ወደ ምስራቅ እጇን ዘርግታ ቆማ ስትጸልይ በቤተክርስቲያ ውስጥ ከደስታ ብርሀን ጋር ያማረ ሽታ መላ ጌታችን ከአዕላፋት መልአክትና ቅዱሳን ጋር ወደ እርሷ መጣ፡፡ እናታችን ቅድስት ፍቅርተ ክርስቶስም ሰገደች፡፡ ተንበረከከች እጅግም አለቀሰች፡፡ ከወደቀችበት ቦታ አንስቶ ‹‹ ላጠፋሽ አልመጣሁም ወዳጄ ላከብርሽ ነው እንጂ›› አላት፡፡የዘለአለም መንግስት አዘጋጅቼልሻለሁ እና ደስ ይበልሽ ፡፡ቅድስት ፍቅርተ ክርስቶስም ቃል ኪዳን እንዲገባላት ተማጸነችው ጌታችንም ‹‹ሁሉም እንደ ቃልሽ ይሁንልሽ በስምሽ ስሜ ተጨምሯልና ለቤተክርስቲያንሽ መባ የሰጠ፣ የተላከ ፣የተቀበረ፣ ቤተ መቅደስሽ መጥቶ የተሳለመ ፣ እስከ 12 ትውልድ የምህረት ቃል ኪዳን ሰጠሁሽ በረከቴም በቤቱና በልጆቹ በገንዘቡም ላይ ይደር የገድልሽ መጽሐፍ ባለበት አጋንንት ሰይጣናት አይቀርቡም በአዝመራ ስምሽን በጠሩት ጊዜ የለመለመ ይሁን በጸሎትሽ የተማጸነ ሁሉ ባለጤና ይሁን ስምሽን በእውነት የሚጠራ የከበረ ነው፡፡ ያለመጠራጠር በቀናች ሐይማኖት የገድልሽን መጽሐፍ የጻፈ ያጻፈ ያነበበ የተረጎመ በሐይማኖት የሰማ እስከ ቀዝቃዛ ውሃ ድረስ የሰጠ ኃጢያቱ ይሰረይለታል፡፤ስለድካምሽ ስለትሩፋትሽ 7 አክሊሎችን እና ይህን ሁሉ ቃል ኪዳን ሰጠሁሽ ፡፡ ላልምረው ቦታሽን አላስረግጠውም›› ብሏት ወደ ሰማይ አረገ፡፡
በማግስቱ ትንሽ ህመም ታመመች ደናግል መነኮሳትን ጠርታ የእረፍት ቀኗ መድረሱን ነገረቻቸው ከመካከላቸው አንዷን ለገዳሙ አስተዳዳሪነት መርጣ በፍቅር ስም ተሰናበተቻቸው፡፡የዳዊት መዝሙርንም ስትጸል የካቲት 29 ቀን እሁድ አጥቢያ ጠዋት በጌታ በዓል አንቀላፋች ነፍሷ ከስጋዋ ተለየች፡፡ ጌታችንም ከእናቱ ጋር ከቅዱሳኑ ጋር መጥቶ ነፍሷን ተቀብሎ ወደ ዘለዓለም ገነት ወሰዳት፡፡ ቅዱሳንም ከመላእክት ጋር እልል እያሉ እያመሰገኑ ወደ ዘለዓለም ቦታ ገነት አስገቧት፡፡ ከቅድስት ፍቅርተ ክርስቶስ መቃብር ላይ 40 ቀናት ብርሃን ሲበራበት ታይቷል፡፡
በሰሜን ወሎ ሀገረ ስብከት በመቂት ወረዳ ጥባ ማርያም ቀበሌ ውስጥ ምን ታምር በመትባል ቦታ ላይ በ16ኛው መቶ ክፍለ ዘመን በኢትዮጵያዊቷ ሰማዕትና ጻድቅ ቅድስት ፍቅርተ ክርስቶስ የተመሰረተቸው እመ ምዑዝ ኪዳነ ምህት ቅድስት ፍቅርተ ክርስቶስ አንድት ገዳምም በዓላቶቿ የሚከበሩት ታህሳስ 16 የቅዳሴ ቤቷ እንዲሁም የካቲት 29 ቀን በዓለ እረፍቷ ይከበራል፡፡

የእግዚአብሔር፣ቸርነት የድንግል ማርያም አማላጅነት፣ የቅዱሳን መላእክት ተራዳኢነት፣ የጻድቃን፣ የሰማዕታት፣
የቅዱሳን ሐዋርያት፣ የቅዱሳን አበው መነኮሳት፣ የቅዱሳት አንስት፣ የደናግላንና የቅዱሳን ሁሉ ምልጃና
ቃል-ኪዳናቸው ባለንበት ከሁላችን ጋር ይሁን ይቆየን፡፡ ወስብሐት ለእግዚአብሔር ለዘበቅዱሳኒሁ ይሴባሕ
ይእዜኒ ወዘልፈኒ ወለዓለም ዓለም አሜን፡፡ ወአሜን ለይኩን ለይኩን፡፡ አነሳስቶ ያስጀመረኝ አስጀምሮ ያስጨረሰኝ
የቅዱሳን አባቶቻችን አምላክ ይክበር ይመስገን አሜን፡፡
ምንጭ፡- ገድለ ቅድስት ፍቅርተ ክርስቶስ
ምንጭ፡- ገድለ ቅድስት ፍቅርተ ክርስቶስ
ጸሀፊ ገዛሀኝ ፈንታሁን
No comments:
Post a Comment