ተወግተው ስለ ሞቱ ስለ ሕዝቤ ሴት ልጅ ሰዎች ሌሊትና ቀን አለቅስ ዘንድ ራሴ ውኃ፥ ዓይኔም የእንባ
ምንጭ በሆነልኝ! ትንቢተ ኤርምያስ 9+1
ለዋኖቻችሁ ታዘዙና ተገዙ፤ እነርሱ ስሌትን እንደሚሰጡ አድርገው፥ ይህንኑ በደስታ እንጂ በኃዘን እንዳያደርጉት፥ ይህ
የማይጠቅማችሁ ነበርና፥ ስለ ነፍሳችሁ ይተጋሉ። ወደ ዕብራውያን 13+17
እኔ ባሪያህ ዛሬ በፊትህ ስለ ባሪያዎችህ ስለ እስራኤል ልጆች ሌሊትና ቀን የምጸልየውን ጸሎት ትሰማ ዘንድ ጆሮህ
ያድምጥ፥ ዓይኖችህም ይከፈቱ መጽሐፈ ነህምያ። 1+4
ሙሴም በእግዚአብሔር በአምላኩ ፊት ጸለየ፥ አለም። አቤቱ፥ ቍጣህ በታላቅ ኃይልና በጽኑ እጅ ከግብፅ ምድር ባወጣኸው
በሕዝብህ ላይ ስለ ምን ተቃጠለ? …………አሁን ይህን ኃጢአታቸውን ይቅር በላቸው፤ ያለዚያ ግን ከጻፍኸው መጽሐፍህ
እባክህ ደምስሰኝ አለ። ዘፍ 32+11-33
ከመዓትህ ተመለስ፥ ለሕዝብህም በክፋታቸው ላይ ራራ። …… ዘራችሁን እንደ ሰማይ ከዋክብት አበዛለሁ፥ ይህችንም
የተናገርኋትን ምድር ሁሉ ለዘራችሁ እሰጣታለሁ፥ ለዘላለምም ይወርሱአታል ብለህ በራስህ የማልህላቸውን ባሪያዎችህን
አብርሃምንና ይስሐቅን እስራኤልንም አስብ። ዘፍ 32+11-33
ብዙ ኀዘን የማያቋርጥም ጭንቀት በልቤ አለብኝ ስል በክርስቶስ ሆኜ እውነትን እናገራለሁ፤ አልዋሽምም፤ ሕሊናዬም
በመንፈስ ቅዱስ ይመሰክርልኛል። በሥጋ ዘመዶቼ ስለ ሆኑ ስለ ወንድሞቼ ከክርስቶስ ተለይቼ እኔ ራሴ የተረገምሁ
እንድሆን እጸልይ ነበርና። ወደ ሮሜ ሰዎች 9+1-3 ወስብሀት ወለአለም አለም አሜን ቸር እንሰንብት
No comments:
Post a Comment