Monday, November 19, 2012

ፃድቁ አባታችን አባ ኪሮስ


“በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ ዘይሴልስ በአካል ወበግብር ወበስም ወይትወሐድ በመለኮት ወበባሕርይ ወበሕላዌ ቅድስት ሥላሴ” ሥላሴ ዕሩይ ኩሉ ጊዜ ይእዜኒ ወዘልፈኒ ወለዘይመድእ ዓለም ለዓለመ ዓለም አሜን የቅዱሳን ሁሉ በረከታቸው ረድኤታቸው አይለየን። አሜን። “ቅዱሳን በመለኮታዊ ማዕጠንት የተቀጣጠሉ ዕጣን ሲሆኑ፤ የተቀጣጠሉበትም በፈጣሪያቸው ፍቅር ነው።” (ብጹህ ወቅዱስ አቡነ ሽኖዳ) አባ ኪሮስ አባቱ ንጉስ ዮናስ እናቱ አንሰራ ይባላሉ፡፡ ሀገሩ ሮም ሲሆን ወላጆቹ እግዚአብሔርን የሚፈሩ ደጋግ ቅዱሳን ነበሩና አቡነ ኪሮስን በታህሳስ 8 ቀን ወለዱት፡፡ ታላቅ ወንድ ቴድሮስ ይባል ነበር፡፡ አባ ኪሮስ የመጀመሪያ ስሙ ዲላሶር ይባል ነበር፡፡ በኋላም አባቱ ከሞተ በኋላ ሃብቱን ከወንድሙ ተካፍሎ ለድሆች መፅውቶ ዓለምን ንቆ መንኖ መኖርን መርጦ ሄደ፡፡ ቅዱሳን ጻድቃን መላ ዘመናቸውን ከጣዕመ ዓለምና ከተድላ ዓለም ተለይቶ ቤት ልስራ ዘር ልዝራ ሳይሉ ፈቃደ ሥጋቸውን ለፈቃደ ነፍሳቸው አስገዝተው በጾም፣ በጸሎት፣ በስግደት፣ በምናኔ ጸንተው የኖሩ ናቸውና፤ ከአባ በቡንዳ ገዳምም ገባ፡፡ በ17 ዓመቱ ስርዓተ ምንኩስናን ተማረ፡፡ በአባ በቡንዳ እጅ መነኮሰ፡፡ ከዚህ በኋላ በፆም በፆሎት ተወስኖ ኖረ ፡፡ ከፀሎት ሲመለስ አባ በቡንዳን አንበሳ ሰባብሮ ገድሎት አየ፡፡ አንበሳውን ተራምዶ አባቱ ቡነዳን ቀብሮ ሲሄድ አንድ ሃብታም ሞቶ እየተበላ እየተጠጣ ጥይት እየተተኮሰ መቃብሩ ደምቆ አየ ፡፡ ተገርሞ ጌታን ዓለምን የናቁ የአንተ ወዳጆች ሞታቸው አያምርም ኣለምን የወደዱ አንተን የጠሉ ሞታቸውና ኑሮአቸው ያምራል፡፡ ይህን ፍረድ ብው 40 ዘመን ተኙ፡፡ እላያቸው ላይ ሳር በቅሎባቸው ሳለ መላእክት መጥተው ተነስ ቢሉት አዳም የፍጡር ቃል ሰምቶ ወድቋል ጌታዬ ድምፁን ያሰማኝ አላቸው፡፡ በኋላ ኪሩቤል አንስተው ወስደው ገነትን አሳይተውት ጌታችንም ቃ ኪዳን ሰጥቷቸዋል፡፡ መካኖች ልጅ የሌላቸው ገድን አዝለው ቢያለቅሱ፣ፀበሉን ቢጠጡ፣ስምህን ቢጠሩ፣የመካኒቱን ማህፀን እከፍታለሁ፡፡ የሚሞትባቸውን እንዳይሞት አደርጋለሁ፡፡ በንፁህ ገንዘቡ ቂምና በቀልን ሳይዝ በሕግ በሥጋውና በደሙ የፀና ሰው በስምህ በተሠራው ቤተክርስቲያን ጧፍ፣ ዘይት፣ ያበራና መገበሪያ ዕጣን፣ዘቢበ፣መንጦላዕት፣መጋረጃ፣ምንጣፍ፣ጥላ፣ ወዘተ ያመጣውን ልጅ እሰጠዋለሁ፡፡ ብሎ ቃል ኪዳን ገብቶለታል፡ ከዚህም በኋላ በተወለደ በ270 ዓመቱ ሐምሌ 8 ቀን አርፏል፡፡ የጻድቁ በረከት ይደርብን፡፡ “ተዘከሩ መኳንንትክሙ ዘነገሩክሙ ቃለ እግዚአብሔር” ዕብ 13፡7 “የእግዚአብሔርን ቃል የነገሩአችሁን ዋኖቻችሁን አስቡ” የእምነታቸውንም ፍሬ እየተመለከታችሁ በእምነት ምሰሏቸው፡፡ ዕብ 13፡7 ስብሐት ለከ አቤቱ በፍጥረት ሁሉ አንደበት የምትመሰገን ላንተ መድኃኔዓለም ክርስቶስ ክብርና ምስጋና ይገባል አቤቱ ለተራቆቱት ልብስ የምትሆናቸው ላንተ ኢየሱስ ክርስቶስ ክብርና ምስጋና ይገባል አቤቱ በመንግስትህ ሽረት በህልውና ሞት ህልፈት የሌለብህ ላንተ ለንጉስ ክርስቶስ ክብርና ምስጋና አቤቱ የቅዱስ አብ አካላዊ ቃል የዓለም ሁሉ መድሐኒት ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ ላንተ ክብርና ምስጋና ይገባል፡፡ በሰማይ ያሉ መላእክት በምድርም የሚኖሩ የአዳም ዘር ሁሉ የሚያመሰግኗት በአማላጅነቷ ሁል ጊዜ የማትለየኝ ከፀሐይ ሰባት እጅ የምታበራ የብርሃን እናት የሁሉ እመቤት የአምላክ እናት ከተመረጡ የተመረጠች ከተለዩ የተለየች ከተከበሩ የተከበረች እናቴ እመቤቴ ድንግል ማርያም በቃላት ልገልጸው ከምችለው በላይ አመሰግናለሁ፡፡ የእግዚአብሔር፣ቸርነት የድንግል ማርያም አማላጅነት፣ የቅዱሳን መላእክት ተራዳኢነት፣ የጻድቃን፣ የሰማዕታት፣ የቅዱሳን ሐዋርያት፣ የቅዱሳን አበው መነኮሳት፣ የቅዱሳት አንስት፣ የደናግላንና የቅዱሳን ሁሉ ምልጃና ቃል-ኪዳናቸው ባለንበት ከሁላችን ጋር ይሁን ይቆየን፡፡ ወስብሐት ለእግዚአብሔር ለዘበቅዱሳኒሁ ይሴባሕ ይእዜኒ ወዘልፈኒ ወለዓለም ዓለም አሜን፡፡ ወአሜን ለይኩን ለይኩን፡፡

No comments:

Post a Comment