Monday, November 19, 2012

ፃድቁ መናኝ ገብረ ክርስቶስ

ጥቅምት 14 ጻድቁ መናኝ ገብረ ክርስቶስ የእረፍቱ መታሰቢያ ቀን ነው በዚሁ ቀን አቡነ አረጋዊም የተሰወሩበት ዕለት ይታሰባል እንዲሁም ሐዋርያው ፊሊጶስ ያረፈበት ዕለት ይታሰባል፡፡ ++++++++የአባቶቻችን በረከታቸው አማላጅነታቸው ይጠብቃን+++++++++ ጻድቁ መናኝ ገብረ ክርስቶስ የንጉሱ የቴዎድዮስ ልጅ ነው፤:: ከጫጉላ ቤት ጠፍቶ መነነ፤ አባቱም ወታደሮችን ላከበት፤ ገብረ ክርስቶስ ሌት ተቀን ተጉዞ የእመቤታችንን ደብር አገኘ ተንበርክኮም እመቤቴ ወታደሮች እንዳይዙኝ መልኬን ቀይሪሊኝ አላት:: የውስጥ ሰውነቱ ተገለበጠ በቁስልም የተመታ ሆነ ደጀ ሰላሙ ላይ ምጽዋት ከሚለምኑ ድሆች ጋር ተቀመጠ የአባቱም ወታደሮች ደረሱበት አ ላወቁትም ምጽዋት ሰጥተውት ያልፋሉ፤ በዚያች በቤተክርስቲያን 15 ዓመት በተጋድሎ ኖረ ከዚያም ወደ አገሩ ተመልሶ በአባቱ ደጅ 15 ዓመት ወድቆ ለመነ:: አባቱ አሸከሮቹን እንዲህ አለ ይህንን ደሃ ምጽዋት ስጡት ልጄ ምናልባት ልክ እንደዚህ ደሃ ሆኖ በሰው አገር እየተንከራተተ ይሆናልና አላቸው:: የአባቱ አሸከሮች ግን የእጅ እጣቢ፤ሽንት ይደፉበት ነበር በላዩ ላይ አጥንት እየወረወሩ ውሾች እንዲጣሉበት ያደርጉ ነበር:: በእንዲህ ያለ ተጋድሎ 15 ዓመት ኖረ፤የእረፍቱ ቀን ጥቅምት 14 ሲደርስ የንጉሱ የቴዎድዮስ ልጅ መሆኑን የደረሰበትን ሁሉ መከራ ጽፎ ይሞታል፤ሊቀብሩት ሲሰበሰቡ ይህችን ጽሁፍ ያገኛሉ:: አባትና እናቱ መሪር ለቅሶ አለቀሱ አገሩ በሙሉ አለቀሰለት ከበድኑ አስገራሚ ተአምራት ተገለጹ ድውያን ሁሉ ተፈወሱ፤በታላቅ ክብርም ቀበሩት፤ +++++++የቅዱሳኑ የአባታችን አቡነ አረጋዊ፡ የጻድቁ መናኝ ገብረ ክርስቶስ እንዲሁም የሐዋርያው ፊሊጶስ በረከታቸው ረድኤታቸው ከሁላችን ጋር ይሁን ለዘላለሙ አሜን ፡፡ 

No comments:

Post a Comment